በ2017 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠና...

image description
- In code inforcement    0

በ2017 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር፣ በመከላከል እንዲሁም እርምጃ በመዉሰድ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ

በ2017 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር፣ በመከላከል እንዲሁም እርምጃ በመዉሰድ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ

8/11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት በማድረግ በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት እውቅና ሰጥቷል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ እንደገለፁት ተቋሙ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት በ2017 በጀት አመት በርካታ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር፣ በመከላከል እንዲሁም እርምጃ በመዉሰድ ከተማችን ብሎም ክፍለ ከተማችን ከደንብ ጥሰት የፀዳች እንደትሆን ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመትም ህገ-ወጥነትን የመከላከል ስራ ተጥናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ደሳለኝ ጠቁመው ለሚሰሩ ስራዎችም ሁሉም የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀው በ2017 በጀት አመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በመያዝ ከነበሩ ክፍተቶች ትምህርት ወስዶ በማረም በ2018 የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የደንብ ጥሰትን ከመከላከል እና ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ተገልጿል።

በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው ምዘና የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና ባለሙያዎች እውቅና የተሰጠ ሲሆን ወረዳ 11, 1ኛ ፣ ወረዳ 1,  2ኛ ፣ ወረዳ 10   3ኛ ደረጃ በመውጣት እውቅና ተሰጥቷቸዋል ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments