
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ
29/11/ 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች የክ/ከተሞችና የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣አጠቃላይ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ የ2017 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ፡፡
በመዶረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበጀት አመቱ ከ27 ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘረጋት፣ ለህብረተሰቡ የደንብ ስርፀት ስራ በመስራት ፣የኮሪደር ልማት በመጠበቅና የወንዝ ዳርቻ ልማትን በማጠናከር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።
በበጀት አመቱ ከአስተዳደራዊ ቅጣት አራት መቶ አራት ሚሊየን ብር በመቅጣት እርምጃ የተወሰደ ሲሆን የደንብ ጥሰት በ69.8 ፐርሰንት መቀነሱን በመግለፅ የከተማ አስተዳደሩም ለባለስልጣኑ የሰጠው እውቅናና ሽልማት ለቀጣይ ስረሠ ብርታት እና ተወዳዳሪነት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰለምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወሮ ሊዲያ ግርማ ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰትን በመከላከልና በመቆጣጠር ከተማዋ በስርዓት እድትመራ በማድረግ ፣ በከተማ አስተዳደሩ የሚወጡ ደንቦችን በማስተግበር፣ ጠንካራ ስራዎችን ማከናወኑ ጠቁመዋል።
ይህንን ውጤት በቀጣይ በጀት አመትም በቁርጠኝነት በማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በእውቅናና ሽልማት መድረኩ ተሸላሚ የሆኑ ክፍለ ከተሞች
1ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
2ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
3ኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሲሆኑ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች፣ አንደኛ ለወጡ 11 ወረዳዎችና ኦፊሰሮች ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በሽልማቱ ከአንድ እስከ 3ተኛ ደረጃ ላገኙ ክፍለ ከተሞች እና ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ ለወጡ 11 ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል፣ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ ለወጡ ከ11ኦፊሰሮች ሰርተፍኬትና የ5 ሺህ ብር ቦንድ እንዲሁም ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድኖች እና ፈፃሚዎች የዋንጫ ሰርተፍኬትና የ5ሺህ ብር ቦንድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments