
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የወርቃማ ሰኞ የእውቅት ሽግግር ማጠቃለያ የማጠቃለያ ፕሮግራም አከናወነ
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የወርቃማ ሰኞ የእውቅት ሽግግር ማጠቃለያ የማጠቃለያ ፕሮግራም አከናወነ
ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዘወትር ሰኞ ጠዋት አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት ልምድና ዕውቀትን የሚጋሩበት የወረቃማ ሰኞ (የአብሮነት መደረክ) ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙት የ2017 በጀት አመት ማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሄደ ።
መድረኩን የከፈቱት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ዝግጅቱ ለሰኞ ቀን የነበረን አመለካከት የተቀየረበት ፤ወርቃማ ሰኞ ሰራተኛው እና አመራሩ በማለዳ ተገኝቶ ልምድና ተሞክሮውን የሚጋራበት ፤ የጋራ ቁርስ ፕሮግራም በማካሄድ ለስራ የሚያነሳሳ መርሀግብር መሆኑን በመጥቀስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የአውትሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን የሚተጋ ፣ የሚታትር ፣ የሚደክም ይሸለማል የተጀመረውን ጉዞ ወደኋላ ሳትሉ በቀጠይም የተቋም ግንባታችሁን እሰከታችኛው እርከን ድረስ በማጠናከርና መልካም አሰተዳደር በመፍጠር ውጤቱን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል ።
አያይዘውም የወርቃማ ሰኞ ፕሮግራም እምቅ የሆነ እውቀት ያላቸው ሰዎችን ልምድ የሚገኝበት አንዱ በአንዱ የሚማርበት መድረክ በመሆኑ በዚህ ልክ ማስኬድ በመቻሉ ባለስልጣኑን ለውጤት ማድረሱን ተናግረዋል።
በዝግጅቱ በባለስልጣኑ የስታንዳርድዜሽንና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀፀላ አማከኝነት በ2017 በጀት አመት በወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም መከናወን ያስገኛቸውን ውጤቶች ፣ የተከናወኑ ተግባራትን እና በ2018 በጀት በምን መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የሚያሳይ ሰነድ ቀርቧል።
በመርሀ ግብሩ በቀጣይ በምን መልክ መቀጠል እንዳለበት ውይይት የተደረገ ሲሆን 2017 በጀት ዓመት በተከናወኑ የወርቃማ ሰኞ ፕሮግራሙ አቅረቢዎች በተመለከተ የተዘጋጀ አጭር የፎቶ ስላይድ ማሳያ ቀርቧል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments