
ባለስልጣኑ በ2017 አፈፃፀሙ ያገኘውን የእውቅናና ሽልማት በ2018 በጀት አመት ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ተወያየ
ባለስልጣኑ በ2017 አፈፃፀሙ ያገኘውን የእውቅናና ሽልማት በ2018 በጀት አመት ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ተወያየ
ሀምሌ 16/2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተካሄደ ምዘና ከተቋማት ( ካቢኔ አባል ካልሆኑ ) በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንደኛ ደረጃ በማግኘቱ የመኪና ሽልማት መሸለሙን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ማኔጅመንት አባላት ደስታውን በመግለጽ ውጤቱ ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ይህ የዕውቅናና ሽልማት መምጣት የቻለው ከላይ እስከታች የሚገኝ አመራርና ሰራተኛ በትጋት፣ በቅንጅት፣በትብብር በተለይም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በአግባቡ በመወጣቱ በመሆኑ የክፍለ ለከተማ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል ።
አክለውም ውጤቱ ለቀጣይ ስራ አቅም የሚሆን ሲሆን ለውጤቱ መመዝገብ አስተዋጽዎ ላደረጋችሁ የክፍለ ከተማ ና የወረዳ የደንብ ጽ/ቤት ኃላፊዎቹ ሰራተኞችና ኦፊሰሮቻችን በሙሉ ምስጋና በማቅረብ እንኳን ደስ ያላችሁ የድካም ውጤት በመሆኑ ምስጋና ይገባችኋል በማለት ደስታቸውን አጋርተዋል።
የደስታው ተካፋይ የሆኑ የክፍለ ከተማ አመራሮች 2017 በጀት አመት ከፍተኛ ለውጥ የታየበት የከተማ አስተዳደሩን የልማት ስራዎች የተጠበቁበት እና የደንብ ጥሰቶች የቀነሱበት በመሆኑን ውጤቱን ይጠብቁት እንደነበር እና በቀጣይ አመትም ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments