
የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በወረዳ 05 የአቅመ ደካማ እናት የቤት እድሳት አስጀመረ
የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በወረዳ 05 የአቅመ ደካማ እናት የቤት እድሳት አስጀመረ
16/11/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራና ምክትል ስራ አስኪያጆች በተገኙበት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ነዋሪ የሆኑ አቅመ ደካማ ወ/ሮ አስታጥቃ ቢሻው ቤት በ90 ቀን እቅድ ውስጥ አድሶ ለማስረከብ በዛሬው እለት አስጀምረዋል።
ተቋሙ በ90 ቀናት እቅድ ውስጥ የችግኝ ተከላ፣ የማዕድ ማጋራት፣ የደም ልገሳና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የማድረግ ስራዎችን አጠናክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ሻለቃ ዘሪሁን አስታውሰው፤ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅ ደካማ እናት ቤትን በአጭር ቀናት ውስጥ አድሶ ለማስረከብ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም በላቀ ውጤት በማጠናቀቅ ከከተማው አስተዳደር ሴክተር ተቋማት ጋር ተወዳድሮ 1ኛ በመውጣት የመኪና ሽልማት በማግኘቱ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የህብረተሰብ ክፍሎችና አጠቃላይ የተቋሙ አመራሮች፣ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችና ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments