
ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት ከከተማ አስተዳደሩ በተዋቀሩ የምዘና ቡድን አባላት ተመዘነ
ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት ከከተማ አስተዳደሩ በተዋቀሩ የምዘና ቡድን አባላት ተመዘነ
10- 11- 2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ የምዘና ቡድን ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን የሰነድና የተግባር ምልከታ በማድረግ ምዘና ተካሂዷል።
በምዘናው በባለስልጣኑ የተከናወኑ አበይት ተግባራት ፣ከግብ አንፃር የተሰሩ ስራዎች ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ብልሹ አሰራር ከመከላከል፣ለተገልጋይ ምቹ የስራ ቦታ ከመፍጠር የኪፒአይ እቅድ አፈጻጸም፣ የመልካም አስተዳደር፣ የቅሬታ አፈታት እና የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችና ሌሎች ተግባራት በምዘና ቡድኑ ታይተዋል::
በምዘና ቡድኑ የባለስልጣኑን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ዋና ዋና ተግባራት በሰነድ እና በአካል ምልከታ በዝርዝር በማየትና በመመዘን ውጤት ተሰጥቷል፡፡
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments