ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀሙ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀሙ እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀሙ  እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

             8/11/2017 ዓ.ም
         ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ  እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ።

ውይይቱን የከፈቱት  የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በበጀት አመቱ በተዋረድ  ሪፖርቶች እየተገመገሙ አመቱ ማጠቃለያ ላይ መደረሱን ገልፀው በበጀት አመቱም በኮሪደር ልማት ፣በወንዝ ዳርቻ ብክለት፣ በበጎ ተግባራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል ።

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በከተማችን የሚስተዋሉ ደንብ ጥሰቶች በ69.8% እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን የጽ/ቤት ኃላፊው ገልፀዋል ። 

የ2017 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 አመታዊ እቅድ በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

በሪፖርቱ የተቋም ግንባታ ስራዎች መሰራታቸው ፣የስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ በስፋት መሰጠት መቻሉ፣ በከተማዋ የሚታዩ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ህገወጥ ተግባራት መቀነስ መቻሉ የመሳሰሉት በዝርዝር ቀርቧል ።

ባለስልጣኑ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በርካታ በጎ ተግባሮችን ያከናነ ሲሆን በአመቱ 14 /አስራ አራት/ የአቅመ ደካማ ቤት በማደስ ሀላፊነቱን መወጣቱን በሪፖርቱ ተመልክቷል።

የዳይሬክተሩ   የ2018 በጀት አመት እቅድ አስመልክቶ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከመፍታት አንፃር ፣ከተቋም ግንባታ አንፃር ፣የደንብ መተላለፍ የሚፀየፍ ማህበረሰብ ከመፍጠር አንፃር እና የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት ከመከለከልና ከመቆጣጠር አንፃር የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የለውን እቅድ  በማብራራት አቅርበዋል።

በውይይቱ  ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንፃር ፣ ህገወጥ ተግባራት ሙሉ ለሙሉ ከማጥፋት አንፃር እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ላይ ትልልቅ የትምህርት ተቋማት ማካተት ቢቻል  የመሳሰሉት ሀሳቦች አና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ  የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተገኝተው ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ አጠቃላይ የስራ ሂደቱን በሚመለከት ግምገማ መደረጉ በጥንካሬ የተነሱ ሀሳቦችን ይበልጥ በማጠናከር በድክመት የተጠቀሱትን በማስተካከል ለቀጣይ ዕቅድ ግብአት ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀው ውይይቱ ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments