ባለስልጣናኑ ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣናኑ ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የስራ ልምዱና ተሞክሮውን አጋራ

ባለስልጣናኑ ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የስራ ልምዱና ተሞክሮውን አጋራ

              07/11/2017 ዓ.ም
              ****አዲስ አበባ****  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ስለ ተቋሙ አጠቃላይ አደረጃጀትና የስራ እንቅስቃሴዎችን የተመለከተ ልምድና ተሞክሮውን  አጋራ። 

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በተሞክሮ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ተቋሙ የከተማችን ፈጣን እድገት በመገንዘብ በተከናወነው የልማት ስራዎች የራሱን ድርሻ ለመወጣት 24/7 የስራ ባህል አድርጎ ቀን ከለሊት ሳይል በርካታ ስራዎች ማከናወኑንና በዚህም የሚታዩ ውጤት መገኘቱንና ገልፀው የልዑኳን ቡድኑ የተሻሉ አሰራሮችን ወደ ራስ በማምጣት ከዚህ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ 

የተቋም ገፅታ ግንባታ ስራዎችን በማጠናከርና ስትራቴጂካዊ የሆነ የአመራር ስልትን በመንደፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ስራዎችን መምራት በመቻሉ በከተማችን የሚስተዋሉ  የደንብ ጥሰትን  ለመቀነስ መቻሉንአመላክተዋል።

ባለስልጣኑ ከተማችን አዲስ አበባ ጽዱ ውብ ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን የተሰሩ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በአግባቡ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ። 

የጎንደር ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል አስማረ ደምለው ልምምድ ልውውጥ ማድረጉ የተሻሉ አሰራሮችን ተሞክሮዎችን ወስደን ወደ ከተማችን በማምጣት እና በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ በመሆኑ በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ። 

ለልምድ ልውውጥ ለመጡ አካላት የተዘጋጀው መነሻ ሰነድ  በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል። 

በተቋም አደረጃጀት፣በአሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ  በሰነዱ ተመላክቷል፡፡

ለልምድ ልውውጥ የመጡት ቡድኖች ያገኙትን ልምድና ግብዓት መነሻነት በማድረግ ተቋማቸውን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎችን መስራት የሚያስችለን ነው ያሉ ሲሆን ስለ ተደረገላቸው መልካም አቀባበል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከልብ አመስግነዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments