ባለስልጣኑ በሰባዊ መብት አያያዝ እና በስነምግባ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በሰባዊ መብት አያያዝ እና በስነምግባር ዙርያ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በሰባዊ መብት አያያዝ እና በስነምግባር  ዙርያ ስልጠና ሰጠ

                 27/10/2017 
              ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ  የአሰልጣኞች ስልጠና በሰባዊ መብት አያያዝ እና  "ሙስና ስጋት የማይሆንበት ደንብ ማስከበር እንፈጠረ"በሚል በተዘጋጁ ሰነዶች መይ የአሰልጣኞች ስልጠና  ስልጠና ሰጠ። 

የስልጠናውን  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ  አሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ስልጠናው በየክፍለ ከተማቸው ለሌሎች ሰራተኞች በተዋረድ ማሰልጠን  እንደሚገባ አሳስበዋል።

በእለቱ በሰባዊ  መብት አያያዝ  ዙሪያ የተዘጋጀው ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ሰርፀት ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አቃቢ ህግ በሆኑት በአቶ እስጢፋኖስ አበበ ተሰጥቷል ። 

በስልጠናው ስለሰባዊ መብት ምንነት ፣ የሰባዊ መብት ባህርያት ፣ ሰባዊ መብት ከሌሎች በምን እንደሚለይ፣ ሰባዊ መብት ለሰው ልጆች ያለው ጠቀሜታ በዝርዝር ቀርቧል ። 

ከስዓት በኋላ በነበረው የስልጠና ፕሮግራም "ሙስና ስጋት የማይሆንበት ደንብ እንፍጠረ" በሚል የተዘጋጀ ሰነድ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተሰጥቷል። 

በስልጠናው  የሙስና መንስኤ ፣ የሙስና መረጃ  አደረጃጀት እና አቀራረብ የሙስና ጥቆማ አደራረግ፣ ስለ ሙስና ያሉ የህግ ማእቀፎች፣ የጥቆማ አሞላል በመሳሰሉት  ዙሪያ  ከሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ቀርቧል።

በሁለቱም ስልጠናዎች ሰልጣኞች ከስልጠና በፊት የነበራቸውን ግንዛቤ እና ከስልጠናውን  ቡሀላ ያገኙትን እውቀት ለመለየት ፈተና  በመስጠት ስልጠናውን በደንብ ለማስረፅ ተችሏል ።

በመድረኩ የ2017 በጀት አመት በስልጠናና ጥናት እና በግንዛቤ ማስጨበጫ ዳይሬክቶሬት የክፍለ ከተሞች አፈፃፀም  እና የ90 ቀናት ስራዎች በእቅድ መሰረት ስለመከናወን እና ሪፖርት  አደራረግ ላይ ውይይት ተደርጓል። 

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments