
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት ያከናወናቸው የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ልምድ ሊወሰድባቸው የሚገባ መሆኑ ተገለፀ
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት ያከናወናቸው የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ልምድ ሊወሰድባቸው የሚገባ መሆኑ ተገለፀ
26/10/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት አመት በተከናወኑ የመንግስት እና ፓርቲ ተግባራት ላይ በከተማ አስተዳደሩ በተቋቋመ የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት የሰነድና የተግባር ምልከታ በማድረግ ግብረ-መልስ ተሰጥቷል።
ሱፐርቪዥኑ ባለስልጣኑ ለተገልጋይ እና ለሰራተኛው ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ፣ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነትና የተቋም ግንባታ ስራዎች በራስ አቅም ስቱዲዮ በመገንባት መሠራቱ ልምድ ሊወሰድባቸው የሚገባ መሆኑ የሱፐርቪዥኑ ቡድን ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሽታዬ መሐመድ ገልፀዋል።
በመደበኛ ስራው የግንዛቤ፣ የስልጠና ፣የተቋማት ቅንጅታዊ ስራዎች ና ህብረተሰቡ በማሳተፍ የተሰሩ የቁጥጥርና የእርምጃ አወሳሰድ ስራዎች እንደዚሁም የተደራጀ የፓርቲ መረጃዎች ተለይተውና ተሰንደው መቀመጣቸው በሱፐርቪዥን አባላት በጥንካሬ ተነስተዋል::
በመጨረሻም የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሱፐርቪዥን ላደረገው የቡድን አባላት በማመስገን በቀጣይ የበለጠ በመስራት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጣቸው ሀላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ገልፀዋል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments