
ባለስልጣኑ በመንግስት ንብረት አስተዳደር እና በግዢ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ በመንግስት ንብረት አስተዳደር እና በግዢ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
26/10/2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ እና ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመተባበር በግዢ መመሪያ እና በመንግስት ንብረት አስተዳደር ላይ ለማዕከሉ ሰራተኞችና ለአስራ አንዱም ክ/ከተማ የግዢና ንብረት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ስልጠናው በቀጣይ ለምናከናውነው ግዢና ያሉንን ንብረቶች በአግባቡ ማስተዳደር እንድንችል የሚያግዝ በመሆኑ በትኩረት መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በመንግስት ንብረት አስተዳደር ዙሪያ የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በአቶ ኪዳኑ ፈለቀ ቀርበዋል ።
በሰነዱ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ፣የስቶክ አስተዳደር ስርዓት ፣ የመንግስት ንብረት አወጋገድ እና የተሽከርካሪ ስምሪትና አጠቃቀም በዝርዝር ቀርቧል።
በመንግስት ግዢ አፈጻጸም ዙሪያ የስልጠና ሰነድ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ ደሴ አደም ቀርቧል።
በመንግስት ግዢ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ማካሄድ የግዢ መርሆችን ፣ የህግ ማዕቀፎችን የተከተለ ቀልጣፋ ውጤታማ የግዢ አፈጻጸም ስርዓት እንዲኖር ማስቻል መሆኑን አቶ ደሴ ገልጸዋል ።
በመድረኩ ለተነሱ ሀሳቦች ጥያቄዎች ምላሽና አስተያየት በአሰልጣኞቹ ተሰጥበቶ መድረኩ ተጠናቋል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments