ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በጋራ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በጋራ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

                   26/10/2017 ዓ.ም 
                 ****የአዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም የማጠቃለያ የግምገማ መድረክ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት የማእከል፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት በዲሊዮፖል ሆቴል አካሂድዋል።

 የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመክፈቻ  ንግግራቸው በበጀት አመቱ የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ ከማስቀጠል እና ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ከመቆጣጠር አንጻር አመርቂ የሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና የተቀላጠፈ ስራ የተሰራበት ውጤታማ አመት እንደሆነ ገልጸዋል።

በመድረኩም ላይ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አቶ ማስረሻ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮ/ል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

በሰነዶቹ ላይ የሁለቱ ተቋማት የማእከል እና የክፍለ ከተማ አመራሮች የተለያዩ ሀሳብ፣ጥያቄና አስተያየቶች በማንሳት ሰፊ ውይይት በማድረግ በተቋማቱ የበላይ አመራሮች አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በግምገማዊ ውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስ/አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበጀት አመቱ ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ እስከ አፈጻጸሙ በየኳርተሩ የገመገምንበት ሀሳቦችን እየከለስን በጥንካሬ የታዩትን ይበልጥ እየሰራን የመጣንበት መንገድ መልካም መሆኑ ተገልጿል።

ከቀረበው ሪፖርት በቀጣይ በክፍተት የታዩትን በአዳዲስ አሰራሮችና  የመፍትሄ ሀሳብ በማምጣት  ለቀጣይ አመት በአቅድ  በማካተት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  የቀጣይ የስራ አቅጣጫን በመስጠት መድረኩን ተጠናቋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments