ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን...

image description
- In code inforcement    0

ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች /focal person/ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች /focal person/ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
           
              25/10/2017 ዓ.ም
               አዲስ አበባ 

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ፎካል ፐርሰኖች በሶሻል ሚዲያ ዜና አዘገጃጀት እና መሰረታዊ የህዝብ ግንኙነት ላይ የስልጠና መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ መሠረታዊና አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በአዲስ ሚድያ ኔትወርክ በቴሌቪዥንና ሬድዮ ፣ በፕሬስ ድርጅት በጋዜጣ አምድ ፣ እንድሁም በተቋሙ ማህበራዊ ሚድያዎች የባለስልጣኑን መረጃ  ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀዋል ። 

በቀጣይም ያለንን የመረጃ ቅብብሎሽ በማጠናከር የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት አንዲሁም የተቋሙን የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። 

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በበኩላቸው ባለስልጣኑ የሚሰጠውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የሚዲያ አግባቦችን በመጠቀም ላይ ይገኛል፤ በተጨማሪም የምስልና የድምፅ ስቱዲዬ በመገንባት የተቋሙን ገጽታ ግንባት ስራዎች አጠናክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ብቸዋል። 

ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የመረጃ ቅብብሎሽ በማጠናከር የተቋሙን ገጽታ በመገንባት ህብረተሰቡ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረውና ህገ-ወጥነትን የሚጸየፍ ዜጋን ለማፍራት የፎካል ፐርሰኖች  ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አማካኝነት   የሚዘጋጁ ሲሆን ስልጠናዎችን ተግባራዊ በማድረግ ሁሉም የመረጃ ባለሙያ ለተሻለ ስራ ብቁ መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል ። 

የስልጠናው ተሳታፊዎች የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የስራ ክፍሎችን ፣ የተቋሙን ስቲዲዮ እንዲሁም በዳይሬክቶሬቱ የተዘጋጀውን የባለስልጣኑ ዓመታዊ ስራዎች በከፊል የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ጉብኝት አካሂደዋል ። 

ለክፍለ ከተማ እና ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የኮሙዩኒኬሽን ፎካል ፐርሰኖች የተዘጋጀው መሰረታዊ የህዝብ ግንኙነት ስልጠና የሬ/ቴ/ህ/ፕ ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ሄኖክ ታደሰ ቀርቧል። 

በተጨማሪም የተግባቦት ክህሎት /communication skill/ የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ ቀርቧል። 

ከዚህ ስልጠና በኃላ ሰልጣኞች በተግባብት ክህሎት ላይ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው ለሚዲያ ግብዓት የሚሆኑ አጫጭር መረጃዎች እንዲያዘጋጁ የሚያግዝ ይሆናል ሲሉ አቶ ምስራች ተናግረዋል ። 

ተሳተፊዎቹ የተቋሙ ኮሙዩኒኬሽን በጉብኝቱ ወቅት ያሳየን ተግባራትና ያመጠው ለውጥ በቀጣይ ለምናከናውነው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የሚያነቃቃና በዕውቀት የተደገፈ ስራ እንድናከናውን የሚያግዝ ነው ሱሉ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃለፊ ተስፋሁን አሉላ እና በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ  ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments