ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ዙር ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ የጉድጓድ ቁፋሮ ዝግጅት አካሄደ

ባለስልጣኑ  "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ዙር ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ የጉድጓድ ቁፋሮ ዝግጅት አካሄደ

            ሰኔ 24/2017  ዓ.ም
           ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ዙር የችግኝ ተከላ የጉድጓድ ቁፋሮ ዝግጅት መርሃ ግብረሰ አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ የዘንድሮ የአሮንጓዴ አሻራ እቅድን ለማሳካት ህብረተሰቡ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት ጠቁመው ይህ ተግባር አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና አሮንጓዴ ለማድረግ ጉሌሄ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልፀዋል።

በእለቱ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ 7ኛ ዙር የችግኝ ተከላ የጉድጓድ ቁፋሮ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል ቃል እየተካሄደ መሆኑን በማመላከት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ጉድጓድ ለመቆፈር የተደረገውን ትብብርና ቅንጅት በመትከልና በመንከባከብም ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ በ7ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከታቀደው በላይ ጉድጓዶችን መቆፈር የተቻለ መሆኑን አንስተዋል።

መርሃ ግብሩ በክፍለ ከተማው በወረዳ 12 አካባቢ በሚገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ የተካሄደ ሲሆን የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ጨምሮ የደንብ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments