
የባለስልጣኑ ብልጽግና ህብረት የ2017 በጀት ዓመት ኮንፈረንስ አካሄደ
የባለስልጣኑ ብልጽግና ህብረት የ2017 በጀት ዓመት ኮንፈረንስ አካሄደ
ሰኔ 20/2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የብልጽግና ፖርቲ አዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፐብሊክና ፍትህ ልዩ ወረዳ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ብልጽግና ህብረት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ በደማቅ ሁኔታ አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህብረቱ ሰብሳቢ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ብልጽግና ፖርቲ በሀገር አቀፍና በከተማ ደረጃ በርካታ የልማትና የሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት የሀገራችን ዕድገትና ልማት እያፋጠነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በመድረኩ ኮንፈረንስ የውይይት መነሻ ሰነድ ቀርቦ በሰነዱ የሃሳብ ጥራት ፤ዘመንና ትውልድ ተሻግሮ የማየት ብቃት ፣ መጪውን ዘመን የሚያውጅ ምግባርና የድህረ እውነታ ተግባቦት የሚሉ ሀሳቦች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በእለቱ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የብልፅግና ህብረት የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ፣የበጀት ዓመቱ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሪፖርት፣የህብረቱ የ90 ቀናት እቅድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ በአባላቱ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
በኮንፈረንሱ ከዚህ በፊት የነበረው የሁለት ቤተሰብ አባላት ቁጥር በመጨመራቸው የቤተሰቡ ብዛት ወደ 3 በማሳደግ አዳዲስ አመራሮች በመሾምና የተጓደሉ አመራሮች በመተካት አባላቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
በመጨረሻም የህብረቱ አባላት ባለ ስድስት አሀዝ የአቋም መግለጫ በማውጣት ኮንፈረንሱ ተጠናቋል።
መረጃው ፡-የባለሥልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments