ባለስልጣኑ በእቅድ እና ሪፖርት ማኔጅመንት ማስተ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በእቅድ እና ሪፖርት ማኔጅመንት ማስተግበሪያ ሲስተም ላይ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በእቅድ እና ሪፖርት ማኔጅመንት ማስተግበሪያ ሲስተም ላይ ስልጠና ሰጠ

            11/10/2017 ዓ.ም
          ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  የእቅድ እና ሪፖርት ማኔጅመንት ማስተግበሪያ ሲስተምን  በተቋሙ ተግባራዊ ለማድአግ ለማዕከሉ  ዳይሬክተሮች እና ቡድን  መሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው እቅድና ሪፖርትን በሶፍት ኮፒ መስራት የሚያስችል እና ስራዎችን በመመዝገብ  የመረጃ ቅብብሎሹን በማዘመን በተዋረድ ሪፖርቶችን  ወደ ፕላን ኮሚሽን ቢሮ የሚላክበት ሲስተም መሆኑን የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ኮነሬል አድማሱ ተክሌ ገልፀዋል።

ስልጠናው በባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ሚሊዮን ከሳሁን ተሰጥቷል።

በስልጠናው እያንዳንዱ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ወደ ሲስተሙ  የሚገቡበት ሂደት ፣ የሚስጥር ቁልፍ አሰጣጥ ፣ ስትራቴጂክ ግቦች፣ ዓላማዎችና ተግባራት ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች (KPI) እቅድ አና ሪፖርት አመዘጋገብ እና በዘመናዊ መልኩ ያለውን የመረጃ ልውውጥ በተመለከተ በማሳያ ቀርቧል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት እቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው በላይ ሲስተሙ አንድ ተቋም ለተቋቋመለት አላማ ትክክለኛው መንገድ በመጓዝ የተቀመጠለትን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል እና የተቋሙ ስራ ትክክለኛ መስመር ላይ መሆኑን እንደሚያሳይ በስልጠናው ላይ ተገኝተው አስገንዝበዋል ።

በዚህም አንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አንድ ምዘናና አንድ እውቅናና ሽልማት የሚለውን የሚለውን አሰራር ለማስተግበር  እንደሚረዳ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በመጨረሻም የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ፕላንና ልማት ቢሮ ለባለስልጣኑ ለሚያደርገው ትብብር ምስጋና በማቅረብ ስልጠናውን ለአመራሩ በመስጠት ሲስተሙ እስከ ክፍለ ከተማ የሚወርድበት መንገድ እንደሚመቻች በመግለፅ ስልጠናው ተጠናቋል ።

ዘገባው ፦ የባለሥልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments