ባለስልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ ከጠቅላላ ፕ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ ከጠቅላላ ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

ባለስልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ ከጠቅላላ ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

              06/10/2017 ዓ.ም
              ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ በተመለከተ የባለስልጣኑ ከጠቅላላ ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ። 

በመድረኩ የባለሥልጣኑ ዋና-ስራ አስኪያጅ ከ2017 በጀት አመት ልምድ በመውሰድ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ መፈጸምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት  እቅዱ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል ። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ 90 ቀናት ዕቅድ  በባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በአቶ ንጋተ ዳኛቸው ቀርቧል ።

በእቅዱ መደበኛ የተቋሙ ስራዎችና ሰው ተኮር ተግባራት ከማዕከል እስከ ወረዳ በተሰኩረት እንደሚከናወኑ በሰነዱ ተመላክቷል።

በተዘጋጀው እቅድ ላይ ሰፊ ውይይቱ የተደረገ ሲሆን በእቅዱ ላይ የተነሱ ጠቃሚ ሀሳቦች በማካተት መሠራተሰ እንዳለበት ተገልጿል ።

መረጃው፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments