ባለስልጣኑ በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር ተግባር እስከ ወረዳፅ/ቤቱ ቸግባራዊ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ

ባለስልጣኑ በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር ተግባር እስከ ወረዳፅ/ቤቱ ቸግባራዊ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ

                 05/10/2017 ዓ.ም
              ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር ተግባር ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ለላቀ የህዝብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ በመሆኑ እስከ ወረዳ ፅ/ቤቱ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ገለፀ ።

በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 አስተዳር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለአገልጋዮችና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር  እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ጽ/ቤቱን በማደስ አስመርቋል።

ጽ/ቤቱን መርቀው የከፈቱት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ወንድወሰን_አብዩ ምቹ እና ጽዱ የስራ አካባቢን  በመፍጠር ቀልጣፍ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ሀላፊው በወረዳው የተጀመረው ተግባር በሁሉም ወረዳዎች እንደሚቀጥል ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments