
ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተባባሪ አካላት ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለጸ
ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተባባሪ አካላት ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለጸ
05-10 -2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ እና ከ119 ወረዳ ብልሹ አሰራርን ለመታገል ለተመለመሉ ተባባሪ አካላት "ብልሹ አሰራርን በጋራ ለመታገል የተባባሪ አካላት ሚና" በሚል መሪ ቃል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅና በመመሪያ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ከስነ-ምግባር ጉደለትና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ እንዲያከናውን የተባባሪ አካላት ሚናቸው የላቀ በመሆኑ ገልጸዋል ።
አክለውም የተቋሙ ሰራተኛና ኦፊሰሩ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰትን ፣ የኮሪደር ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅና የወንዝ ዳር ብክለትን በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ራሱን ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።
በሰነዱ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሁናዊ ያለበት ሁኔታ ፣ ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንጻር የተባባሪዎች አካላት ሚና እንዲሁም የስነ-ምግባርና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል።
ተቋማችን ከብልሹ አሰራርና ከስነ ምግባር ጉድለት በጻዳ መልኩ ሰራዎችን ለማከናወንና አንዳንድ ችግር የሚታይባቸውን አካላት ተጠያቂ ለማድረግ የተባባሪ አካላት ሚና ጉልህ እንደመሆኑ ወጥ በሆነ ሁኔታ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ እዬብ አስገንዝበዋል ።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments