
ባለስልጣኑ ለሲቪክ ማህበራት በወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል በተመለከተ ግንዛቤ ፈጠረ
ባለስልጣኑ ለሲቪክ ማህበራት በወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል በተመለከተ ግንዛቤ ፈጠረ
ግንቦት 3 2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሲቪክ ማህበራት በወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180 /2017 ግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ አካሄደ።
በመድረኩም ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የአካል ጉዳተኞች ማህበር፣የአረጋውያንና የእድር ምክር ቤት አመራሮችና ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በግንዛቤ መድረኩ በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን መሪ የሆኑት በአቶ ደመረ በለጠ በሰነድ ደንቡንና የቅጣት እርምጃው በዝርዝር ቀርቧል።
በመድረኩ ደንብ መተላለፍ መከላከል እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካም ጌታሁን በከተማችን አዲስ አበባ የሚገኙ ወንዞች ከብክለት ነጻ እንዲሆኑ ባለስልጣኑ እና ከተማ አስተዳደሩ በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ልማት በመጠበቅ ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አበክረው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ የባለስልጣኑ የቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል በከተማው የደንብ ጥሰቶች በተመለከተ ለህብረተሰብ በግንዛቤ በመፍጠርና መረጃ በመስጠት ለተቋሙ ተባባሪ እንዲሆኑና እራሳቸውንም ከደንብ መተላለፍ እንዲቆጠቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም በመድረኩ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments