ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእው...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር አከናወነ

ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር አከናወነ

                  02-10 -2017 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡ 

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ  ኦፊሰሮች ምርቃት ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከስልጠናው ሂደት ጀምሮ እስከ ምርቃት ፕሮግራም መሳካት የበከሉላቸውን ላበረከቱ አካላትና ለመላው የደንብ ማስከበር ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። 

የወርቃማ ሰኞ መድረክ  ሳምንቱን ንቁ ሆነን ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን መልካም ምኞት በመለዋወጥ እርስ በእርሳችን ምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት መሆኑን ገልጸዋል ። 

በዕለቱ የባለስልጣኑ  የኢንስፔክሽን እና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ አባትነህ ውባለም የራሳቸውን የህይወት፣ የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል። 

በተጨማሪም የተቋም ግንባታ ምንነት በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በማቅረብ እውቀት አጋርተዋል ። 

ውጤታማ የተቋም ግንባታ የረጅም ጊዜ ስኬትን ለማስመዝገብ፣ አዎንታዊ ግንኙነትን ለመፍጠር እና ለሰራተኞችም ሆነ ለማህበረሰቡ የበለጸገ አከባቢ ለመፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አቶ አባትነህ አስረድተዋል ። 

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments