
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሁለት ወራት ያሰለጠናቸው ደንብ አስከባሪ ኦፊሰሮችን አሰመረቀ
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሁለት ወራት ያሰለጠናቸው ደንብ አስከባሪ ኦፊሰሮችን አሰመረቀ
30/09/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከ2ሺህ በላይ የ6ተኛ ዙር ደንብ አስከባሪ ኦፊሰሮችን ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የካቤኔ አባላላታቸው በተገኙበት በድምቀት አስመረቀ።
ሰልጣኞቹ ላለፉት ሁለት ወራት በንድፈ-ሃሳብ እና በወታደራዊ ስልጠና በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ አፓስቶ ካምፓስ ሰልጥነው በብቃት ማጠናቀቃቸውን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ የዛሬ ተመራቂዎች የትምህርት ደረጃቸው ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆኑ 2074 ኦፊሰሮች መሆናቸውን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አሳውቀዋል።
ሰልጣኞቹ ለ192 ሰዓታት የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እና ለ239 ሰዓታት የወታደራዊ ስልጠና በማካሄድ በድምሩ ለ431 ሰዓታት 2074 ተመራቂ ኦፊሰሮች ስልጠናው በሚፈለገው ዲስፕሊን መሠረት አሰልጥኖ ለምረቃ ብቁ ማድረጉን የኢትዮጵያ ፈደራል ፓሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ጀነራል መስፍን አበበ አስታውቀዋል።
ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅሙን እያላቀ ከተማ አስተዳደሩ በሚፈልገው ልክ ተልዕኮውን እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብር ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሲሆን ትልቅ መሰጠትና ብቃት ለሚጠይቀው የመስክ ስራ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ ከተማችን አዲስ አበባ እያስመዘገበች ባለችው ሁሉን አቀፍ ልማት ለነዋሪዎቿ ምቹ እየሆነች ነው።
ይህንንም ልማት በህግና ደንብ መመራት እንዲችል በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በሎጀስቲክ በመደገፍ ላይ እንገኛለን።
ከተማዋ በቀን ብቻ ሳይሆን በምሽትም ጭምር እንቅስቃሴዋ ያልተገደበ እንዲሆን ደንብ አስከባሪ ኦፊሰሩን በሶስት ሺፍት በማሰማራት ህግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ ለመስራት አቅጣጫ መቀመጡን ገልፀዋል።
በህዝብ ዘንድ ክብር የሚጎናፀፍ አገልግሎት ለመስጠት በዲሲፕሊን ታንፃችሁ ህዝባችሁን በማሳተፍና በማስተባበር ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እያልኩ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል።
ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments