
እንኳን ለ1446ኛው አረፋ/ለዒድ አል-አድሐ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!!
እንኳን ለ1446ኛው አረፋ/ለዒድ አል-አድሐ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል-አድሐ/አረፋ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! እያለ ባለስልጣኑና በራሴ ስም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።
የአረፉ /ኢድ አል-አድሐ/ በዓል የሰላም ፣የጤና ፣የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንዲሆንልን እየተመኘሁ ህዝበ ሙስሊሙ በበዓሉ ወቅት በአብሮነትና በመተሳሰብ ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት ያለውን በማካፈል በአሉን በማክበር በተለመደው አብሮነት ስሜት እንዲያከብር አደራ እላለሁ ።
ባለስልጣኑ በአሉን አስመልክቶና ማንኛውም በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ስራ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ እንደተለመደው በንቃት እንዲሳተፍና በአክብሮት እጠይቃለሁ።
አዲስ አበባ ከተማችንን የደንብ መተላለፍ የማይስተዋልባት፤ ለነዋሪዎቿና እንግዶቿ ምቹ እንድትሆን ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በመስጠት የበኩሎን እንዲወጡ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
በራሴ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤት ስም መልካም በዓል እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።
ዒድ ሙባረክ!
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ!
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments