
ለኢትዮጵያ ብልፅግና የመንግስት ሰራተኛው ተሳትፎ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
ለኢትዮጵያ ብልፅግና የመንግስት ሰራተኛው ተሳትፎ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
28/9/2017
****የአዲ ስአበባ****
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በከተማ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ስልጠና ከማዕከል አመራርና ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ።
የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው መንግስት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ውይይቶቹ መንግስትና ህዝብን ለማቀራረብ አስፈላጊ በመሆናቸውና ከውይይት የሚጨመቁ ሀሳቦች ፓሊሲዎችን ስትራቴጂዎች ሊቀይሩ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
የመወያያ ሰነዱ በይዘት ሀገራዊ ለውጥ ያስመዘገባቸው ውጤቶችና የሲቪል ሰርቫንቱ ሚና፣ የሲቪል ሰርቪስ አሁናዊ ሀኔታ፣ የአመራር ሁኔታ፣ የመንግስት ሰራተኛ ሁኔታ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሲቪል ሰርቫንት ሪፎርም እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ የመሳሰሉትን ዋና ዋና ይዘቶች ለማየት ተችሏል።
በሰነዱ በአዲስ አበባ ውስጥ ከ70ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ሲኖሩ እነዚህ ሰራተኞች አሁን ላለው ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን በተለይም በትምህርት ፣ በጤና ፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በኮሪደር ልማት በመሳሰሉት ከተማ አቀፍ ስራዎች ሚናቸው ጉልህ መሆኑ ተገልጿል።
በውይይቱ የኑሮ ውድነት ላይ ስርነቀል ስራ መሰራት እንደሚገባ ፣ገበያ ማረጋጋት ምርቶችን ቀጥታ ከገበሬው የሚያገኝበት መንገዶች ቢመቻች፣ የቤት አቅርቦት ለመንግስት ሰራተኛው ቢታሰብበት፣ የትምህርት እድሎች ሰፋ ባለ መልኩ ቢዘጋጅ እና የሰራተኞች የፐብሊክ ትራንስፖርት እጥረት የመሳሰሉት ጉዳዮች በውይይቱ ተነስተዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ሰራተኛው ከብልሹ አሰራር ችግር በመውጣት ህብረተሰብን ወጥ በሆነ መንገድ ማገልገል እንደሚገባ አና ለመንግሥት ሰራተኛውም ምቹ ሁኔታዎች ሊፈጠረለት እንደሚገባ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ገልጸዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን በማዘመን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝና ከላይ የተነሱ ጥያቄዎችን በየደረጃው ለመፍታት ሰፊ እርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ አመላክተዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments