የ6ተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለምረቃ አዲስ...

image description
- In code inforcement    0

የ6ተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለምረቃ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ገቡ።

የ6ተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለምረቃ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ገቡ። 

                    27/09/ 2017 ዓ.ም
                     ****አዲስ አበባ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር  ባለስልጣን የ6ተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በአዲስ አበባ ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሲደርሱ የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች  በተገኙበት አቀባበል ተደረገላቸው። 

የ6ተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አፓስቶ ካምፓስ ሲሰጥ የቆየዉን የሁለት ወር የወታደራዊና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና አጠናቀው ለምርቃት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በሰላም መድረሳቸውን የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል።

አክለውም ስልጠናው ለሁለት ወራት የተሰጠ ሲሆን እጩ ኦፊሰሮችም ቀን ከሌሊት በመትጋት ለምርቃ ብቁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ/በአፖስቶ ካምፖስ/ ሲሰጥ የቆየው የ6ተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ሰልጣኞችም በንድፈ-ኃሳብና በወታደራዊ ስልጠናዎች ምዘናዎችን በብቃት አጠናቀው ለተልዕኮ ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁት ባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ናቸው።

ከስልጠናው በኃላ ለስራው በቂ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የንድፈ ሀሳብና የወታደራዊ ፈተናዎችን ወስደው በብቃት በማጠናቀቅ 

በትላንትናውም ዕለት የባለስልጣኑና የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች፣  የዩኒቨርስቲው መምህራኖች ፣ ወታደራዊ አሰልጣኞች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት የስልጠናው ማጠቃለያ ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም መደረጉን አቶ ንጋቱ አሳውቀዋል። 

ኦፊሰሩ ባገኘው እውቀትና በተሰጠው ስልጠና መሰረት በቀጣይ በከተማችን ላይ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል  ከተማችን እንደ ስሟ አዲስ አበባ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን የስነ-ልቦና ዝግጅት አድርጎ እንዲሰማራ አቅጣጫ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ናቸው።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments