
የባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በተመለከተ የሽኝት እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ
የባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በተመለከተ የሽኝት እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ
26/09/2017 ዓ.ም
**ይርጋለም/አፖስቶ/**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ ለሁለት ወራት በወታደራዊ እና ንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎች ሲያሰለጥናቸው የቆየው እጩ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የመሸኛ ዝግጅት እና በስልጠናው አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስጋና እና የእውቅና መርሀ-ግብር ተካሂድዋል።
በምስጋና ዝግጅቱ ላይ የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በየደረጃው በመገኘት በስልጠናው ሂደት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ስ/አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሀገሪቱ ህግና ደንብ እንዲከበር የበኩልን አስተዋጽኦ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ እና ለዚህም ማሳያ በየዙሩ ሰልጣኞችን በብቃት እያሰለጠነ እንደሚገኝ በመግለጽ በ6ኛ ዙር የኦፊሰሮች ስልጠና ላይም ይኸው ተግባር መቀጠሉን በማንሳት ለሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ ከስልጠናው ባገኙት እውቀት በተግባር በማዋል በቀጣይ ብቁ እና ሀላፊነቱን የሚወጣ ኦፊሰር በመሆን ተቋሙ የሚጥልባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል።
በእለቱም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ ውስጥ በ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ሰልጣኝ ኦፊሰሮች የተገነባ መዝናኛ ቤት ተመርቆ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አስረክቧል።
በሳምራዊት ዘሪሁን
ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments