
የከተማዋ ነዋሪዎች ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራትና ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ
የከተማዋ ነዋሪዎች ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራትና ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ
ግንቦት 23/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙ ከከተማው ነዋሪዎች ጋር የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውይይት አካሄደ።
የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት በባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የከተማችን ሰላምና ልማት ወዳድ ህዝብረተሰብ በማሳተፍ ከተማችን የደንብ መተላለፎች የቀነሰባትና ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን በርካታ ውጤታማ ስራዎች ማከናወናቸው ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች በመጠበቅ እንዲሁም በከተማወ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
በመድረኩ የባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የባለስልጣኑ የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮሎኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በእለቱ የወንዞች ዳርቻ ልማት ለመጠበቅ የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 በተመለከተ ዓላማዎቹ፣ የወጡ ዝርዝር ቅጣቶችና መደረግ ያለበት የመፍትሄ አቅጣጫዎች በግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ በወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በሰነድ በማቅረብ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በመድረኩ የደንብ ባለስልጣን ቀድሞ ከነበረበት አሠራሩና አደረጃጀቱ በማሻሻል አሁን ላይ እየሰራቸው ያሉትን ውጤታማ ስራዎች የልማቱ ባለቤት የሆነው ህብረተሰብ ምስክርነት የተመሠከረበት መድረክ መሆኑን ገልፀዎል።
አክለውም ህብረተሰቡ አሁነሰ ላይ ያለውን እገዛ በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በበኩላቸው ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራታችን ለውጦች መጥተዋል፤ ይህንንም በትልልቅ መድርክ ላይ ከነዋሪው ህብረተሰብ በሚሰጡ አስተያየት ማረጋገጡ አመላክተዋል።
ምክትል ስራ አስኪያጁ ወደፊትም ከናንተ ጋር ስራዎችን አጠናክረው በመቀጠል ባለስልጣኑን ከፍ ወዳለ ደረጃ በማድረስ ከተማችን ከህገወጥ እናፀዳለን ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጊዜ ወደጊዜ እራሱን እያጠናከረና አሰራሩን እያሻሻለ በመምጣቱ የከተማ አስተዳደሩና የማህበረሰቡ አለኝታ መሆኑ መቻሉ ገልፀዋል።
ተሳታፊዋቹ ለኦፊሰሮች ቀንና ሌሊት በሁሉም የልማት፣የፀጥታና በጎ-ተግባራት ላይ እየተሳተፉ በመሆኑ ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ገልፀዋል።
የከተማው ነዋሪዎች አዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሚያከናውናቸው ማንኛውም ተግባራት በሚያስፈልገው ሁሉ አብሮ ለመስራትና ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በቀረበው አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን መድረኩን ሲመሩት በነበሩት ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments