ባለስልጣኑ ለ3 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ለ3 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

ባለስልጣኑ ለ3 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

        22/09 /2017 ዓ.ም
           ****አዲስ አበባ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ  ሲቪለሸ ሠራተኞች በአንደኛና በሁለተኛ ዙር በአጠቃላይ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ።

ስልጠናው በአሰልጣኝ ቢንያም አብረኃ በጊዜ አጠቃቀም፣ ውጤታማ የቡድን ትብብር ችሎታ እና የራስ ተነሳሺነት፣ እራስን ማስተዳደር እና ሌሎች ርዕሶች ላይ በምዘና የታጀበ ውጤታማ ስልጠና ተሰጥቷል። 

በስልጠናውም ላይ ተሳታፊዎቹ የሰጡት አስተያየት በእውቀት፣ በአመለካከትና በክህሎታችን ላይ ስር ነቀል የሆነ ለውጥ የሚያመጣ እና ያገኘነው ስልጠናም በፈተና ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ ውጤታማ ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ  የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና  ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተገኝተዋል።

አቶ ንጋቱ እንዳሉት ተቋሙ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የአቅም ግንባታ ስራ ላይ እየሠራ እንደሚገኝና በእውቀት በአስተሳሰብና ክህሎት የበቃ ባለሙያ ለተቋም ለውጥ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ሰልጣኞችም ተቋሙ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ያቀረበውን ስልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ በአፈፃፀማችን ላይ የሚታይ ተጨባጭ ለውጥ በማስመዝገብ ለህብረተሰባችን የተሻለ አገልግሎት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

በዚህ ቴክኖሎጂ በዘመነበት ክፍለ ዘመን ላይ እንደመገኘታች መጠን በተለያዩ የኦን ላይን ኮሮሶች ጭምር እራሳችንን በማብቃት በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪና ብቁ  ባለሙያ ልንሆን ይገባል፤ በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments