
ሕብረተሰቡን በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ።
ሕብረተሰቡን በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ።
22/09/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮና ንፋስ ስልክ ላፍቶና አራዳ ክፍለ ከተማ አመራርና ኦፊሰሮች ጋር በስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተመለከተ ግምገማዊ ስልጠና መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራና ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
"የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በሁሉም ረገድ እየዘመነች ያለች ከተማን ደንብ መተላለፍ በአግባቡ ለመከላከል እና ህብረተሰቡን በታማኝነት ለማገልገል ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሌም በስነ-ልቦና ዝግጁ በመሆን ተልዕኳችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
በቅርቡ አስመርቀን ወደ ስራ የምናሰማራቸውን የ6ተኛ ዙር ኦፊሰሮቻችንን ጨምረን የሰው ኃይል አቅማችንን የበለጠ በማጠናከር ሕገ-ወጥነትንና የደንብ መተላለፍን በአስተማማኝ መልኩ የምንከላከል ይሆናል ብለዋል።
ሁሉም ኦፊሰር በተመደበበት ቀጠና ላይ በሰዓቱ በመገኝት ከስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ ተልእኮውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በትላንትናው ዕለት ከተቀሩት ክፍለ ከተማ ኦፊሰሮችና አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት መካሄዱ ይታወሳል።
መረጃው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments