ኦፊሰሩ ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ የደንብ ጥሰ...

image description
- In code inforcement    0

ኦፊሰሩ ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ የደንብ ጥሰትን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ ።

ኦፊሰሩ ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ የደንብ ጥሰትን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ ።
  
                  21/ 09/2017 ዓ.ም
                     ****አዲስ አበባ****   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለአዲስ ከተማ ፣ ቂርቆስ እና ልደታ ክ/ከተማ  ከሚገኙ ኦፊሰሮች  ጋር ግምገማዊ የስልጠና መድረክ አካሄደ። 

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ7/24 ቀን ከሌሊት አመራሩና ኦፊሰሩ ተቀናጅቶ በመሰራት በከተማችን ፈጣን እድገት ላይ ተቋማችን የበኩሉን ሚና በብቃት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። 

የዛሬው ስልጠና ለቀጣይ ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራት የሚያግዝ በመሆኑ በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበዋል ። 

በከተማችን ውስጥ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን አስቀድመን መከላከል እንዲሁም ሁሉም አካል ራሱን ከብልሹ አሰራር መቆጠብ እንደሚገባ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ። 

የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና በሚል የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ  በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል። 

በአንዳንድ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ላይ የሚታዩ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግሮችን በመቅረፍ በአዲስ መንፈስና በመልካም የስራ ተነሳሽነት በቅርቡ ተመርቀው ወደ ሰራ ከሚገቡት ከ6ኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር በመቀናጀት በመንግስትና በህዝብ የተጣለባችሁን ኃላፊነት በብቃት የሚወጣ ሃይል ልትሆኑ ይገባል ሲሉ አቶ እዮብ ተናግረዋል። 

የመድረኩ ተሳታፊ ኦፊሰሮች እንደተናገሩት የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነው። 

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል። 

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክላስተር የካ፣ ቦሌ ፣ ለሚ ኩራ እና ጉለሌ ክ/ከተማ የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና በሚል መሪ ቃል የስልጠና መድረክ አካሂደዋል ስልጠናው በሶስተኛ ክላስተር ለተቀሩት ክ/ከተማዎች በነገው ዕለት የሚቀጥል ይሆናል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments