የስነ-ምግባር ችግሮችና ብልሹ አሰራርን መከላከል...

image description
- In code inforcement    0

የስነ-ምግባር ችግሮችና ብልሹ አሰራርን መከላከልና መፀየፍ እንደሚገባ ተገለፀ

የስነ-ምግባር ችግሮችና ብልሹ አሰራርን መከላከልና መፀየፍ እንደሚገባ ተገለፀ
  
                  20 - 09 - 2017 ዓ.ም
                   ****አዲስ አበባ****   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት የባለስልጣኑ እና የክ/ከተማ አመራሮች በተገኙበት ከ119 ወረዳዎች ሽፍት አስተባባሪዎች ጋር ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ተካሄደ ። 

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ  ተቋሙ ራሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ የገጽታ ግንባታ ስራዎችን በማጠናከር ፣ ብልሹ አሰራርን በመታገል ፣ የኦፊሰሩን ሙያዊ አቅም በማጠናከርና አዲስ የፖራ ሚሊተሪ ኃይል መልምሎ በማሰልጠን ከተማችን ከደንብ ጥሰት የጸዳች ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል ። 

አክለውም ብልሹ አሰራር ሌብነት እንደ ሀገር ፣ ከተማ እና ለተቋማችን ገጽታ ግንባታ ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ በመገንዘብ ሁሉም አካል ሊከላከለውና ሊጸየፈው እንደሚገባ ገልጸዋል ። 

የስነ-ምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል ለሽፍት አስተባባሪዎች የተዘጋጀው የስልጣንና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል። 

ሽፍት አስተባባሪዎች ያለውን የስራ ጥንካሬ በማስቀጠል እና አንዳንድ የሚስተዋሉ የስነ-ምግባር  ክፍተቶችን በማስተካከልና በማሻሻል በቀጣይ ስልጠናውን ጨርሰው ወደ ስራ የሚቀላቀለውን የፖራ ሚሊተሪ ኃይል ለመቀበልና ከብልሹ አስራር የጸዳ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ተገልጿል ። 

የመድረኩ ተሳታፊዎች ከአመራሩ የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣትና ብልሹ አሰራርን ለመታገል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ። 

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል ። 

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments