ብልሹ አሰራር ለመታገል የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መ...

image description
- In code inforcement    0

ብልሹ አሰራር ለመታገል የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ብልሹ አሰራር ለመታገል የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

           19/09/2017 ዓ.ም
           ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለማዕከል፣ ክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች ብልሹ አሠራርን ለመታገል የአመራሩ ሚና የላቀ መሆኑን የሚገልፅ የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

ሳሬም ሆቴል አዳራሽ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት የስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራርን ለመታገል ሁሌም አመራሩ ግንባር ቀደም በመሆን ታግሎ የሚያታግል ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በባለስልጣኑ ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ መነሻ የሆነ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይትና ምክክር ተካሄዶበታል።

በስልጠናው ተሳታፊዎችም  የተለያዩ ሃሳብና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን መሰል ስልጠናዎች ለስራ ቅልጥፍና እና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ያለው ሚና የላቀ በመሆኑ መሠል ስልጠናዎች ተጠናክሮ መቀጠል እዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በማጠቃለያው እንደተናገሩት ከላይ እስከ ታች ድረስ ያለው አመራር አስቀድሞ ተቋሙን መውደድና በእኔነት ስሜት ለፈፃሚው ስራን ማውረድና ግልፅና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ተግባሩ መከናወኑን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተከናወኑ ተግባራትን በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግና ማንኛው ከተቋሙ አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣን አካል በፍፁም ሰብአዊነት ማገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም በዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ጠናቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments