
በኮሪደር ልማት ደህንነት ጥበቃ የታየውን መልካም ስራ በወንዝ ዳርቻ ብክለትና መከላከል ላይ ማስቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።
በኮሪደር ልማት ደህንነት ጥበቃ የታየውን መልካም ስራ በወንዝ ዳርቻ ብክለትና መከላከል ላይ ማስቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።
ግንቦት 19/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ፣አባገዳዎች ፣ ሀዳ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ አርቲስቶች ፣ የብሎክ አደረጃጀት ሀላፊዎች እና ለየተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
መድረኩ በሀይማኖት አባቶና በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ከተማ አስተዳደሩ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ልማት ከብክለት በመከላከል የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆኑና በጤና ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ለማስቆም ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ጠቅሰዋል።
በመድረኩ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ከ70 በላይ ወንዞች ሲኖሩ ከመርዛማ ኬሚካል፣ ከመፀዳጃ ቤት ፍሳሾች እና ከበካይ ቆሻሻዎች መከላከል ደህንነታቸው ለማስጠበቅ ደንብ 180/2017 መውጣቱ አስታውቀዋል።
ስልጠናው በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደመረ በለጠ በሰነድ ቀረቧል።
በስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት፣ በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ፣ መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 የተደነገጉ አስተዳደራዊ እርምጃዎ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በስልጠናው ተሳታፊዎች ባለስልጣኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት የከተማዋ የጀርባ ኦጥንት በመሆኑን በተለይ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል ላይ ተቋሙን በማገዝ የድርሻቸው እደሚወጡ ቃል ገብተዋል።
በእለቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ ባለስልጣኑ የቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል እና በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ መሠጠቃለያ የወጣው ደንብ ተግባራዊነት የህብረተሰብ እገዛ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬ ስልጠና መድረክ ተሳታፊዎች ለአካባቢአቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ እንዲፈጥሩ መልእክት ተላልፏል።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments