የወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያ...

image description
- In code inforcement    0

የወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጠረ

የወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት  ዙሪያ  ግንዛቤ ተፈጠረ

              18/09/2017 ዓ.ም
                * አዲስ አበባ *

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዝና የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር  180/2017 ለሲቪክ ማህበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በደንቡ 180/2017 ዙሪያ በተለያዩ   መድረኮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በተደጋጋሚ መሰጠቱን እና ግንዛቤ እንደሚቀጥል በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ።

"የወንዝ እና ወንዞች ዳርቻ ብክለት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ  የህግ  ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ኮርሳ አቅርበዋል።

በሰነዱ በከተማዋ 76 ወንዞች መኖራቸውና የወንዞች ፅዳት ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት በመፍጠራቸው ንጽህናቸው ለመጠበቅ ደንቡን መውጣቱ ገልጸዋል። 

የወንዞች ደህንነት ለማስጠበቅ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዚሁ ዙሪያ ጥናት ማጥናቱን ገልጸው ይህንን ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ ከ2 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ የቅጣት መጠን መቀመጡንም አስታውቀዋል።

የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ስራዎች ለመስራት ከሲቪክ ማህበራቱ እገዛ እንደሚያስፈለግ እና ሲቪክ ማህበራቱ በደንብ ቁጥሩ ላይ የተሰጣቸው ስልጠና በሚኖሩበት አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች  እንዲያስገነዝቡ መልዕክት ተላልፏል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋረ  ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባውን:- የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments