
በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ በሚል ርዕስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ
በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ በሚል ርዕስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ
ግንቦት 15/2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የተዘጋጀው ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች ፣ የሰራ ሂደት አስተባባሪዎች እና ባለሙያዎች ለተካታተይ ሶስት ቀናት በባለስልጣኑ መሰብሰብያ አዳራሽ ሲሰጥ የነበረው በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡
ስልጠናውን ከኤኒ አይ ኮንሰልታንሲ በመጡ የማኔጅመንት አማካሪ በሆኑት በአቶ ቢኒያም አብርሃ የተሰጠ ሲሆን በዋናነት ሰለ ጊዜ አጠቃቀም ፣ ሰለ ውጤታማ የቡድን ትብብር ችሎታ እና የራስ ተነሳሺነት በሚሉ አርዕስቶች የቡድን ስራዎች ውጤት ፣ አቅምን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል ፣ እውቀትን ፣ አመለካከትን አና ክህሎትን በማሳደግ አቅምን መገንባት በሚያስችል መልኩ ቀርቧል፡፡
በስልጠናው ሰልጣኞች በቡድን በመወያየት፤ የተወያዩበትን ሀሳብ መልሰው በማቅረብ እርስ በእርስ በመማማር የሰለጠኑት ስልጠና ላይ ፈተና በመውሰድ በቂ ግንዛቤ እና እውቀት እንዲያገኙ በሚያደርግ መልኩ ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ-አስኪያጅ አቶ ንጋቱ አዳኛቸው ስልጠናው ለስራ አቅም የሚፈጥር ልምድና ተሞክሮ የምናካብትበት ከራስ ጋር የተገናኘ ስለጠና በመሆኑ በብዙ እንዳተረፈችሁበት በመሆኑ በቀጣይ የበለጠ በማንበብ የራስ ጥረት መጨመር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም ሰልጣኞች የተሰጠው ስልጠና ለስራም ይሁን ለራስ የሚጠቅም እራስን ለማየት የሚያስችል በመሆኑ ስልጠናውም አሳታፊ በሆነ መልኩ በጥሩ አቀራረብ ስለተሰጣቸው ለባለስልጣኑ ምስጋና በማቅረብ ቀጣይነት ቢኖረ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments