
ለባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ሰልጣኝ ኦፊሰሮችን በሀገራዊ አንድነት እና መሰረታዊ የመደመር ጽንሰ ሃሳብ ላይ ገለጻ ተደረገ
ለባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ሰልጣኝ ኦፊሰሮችን በሀገራዊ አንድነት እና መሰረታዊ የመደመር ጽንሰ ሃሳብ ላይ ገለጻ ተደረገ
16/09/2017 ዓ.ም
ይርጋለም/አፖስቶ/
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን 6ኛ ዙር እጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮችን በሀገራዊ አነድነት እና መሰረታዊ የመደመር ጽንሰ ሃሳብ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፖስ ኃላፊ እንዲሁም የባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ ገለጻ ተደረጓል።
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የመደመር እሳቤ መነሻ ሃሳብ እንዲሁም አቶ ተፈራ ሞላ የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ስራአስኪያጅ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ ም/ቢሮ ኃላፊ የለውጥ ቀጣይነት እና የፓርቲ ሚና በሚል ርዕስ ሰነድ ለሰልጣኞቹ አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ የቀረበው ሰነድ በመደመር ህሳቤ እና ለውጥ ላይ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋላቸው ገልጸው ገለፃው በቀጣይ ተቋሙ የሚጥልባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት እንዳዘጋጃቸው ገልጸዋል።
ከውይይቱ በመቀጠል ከመድረክ ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ ለሚሰጣቸው ኃላፊነት የተናጠል ህይወት መርህ ተላቀው በአንድነትና በመተባበር የመደመር እሳቤን በመከተል በጋራ በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል።
ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments