በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ...

image description
- In code inforcement    0

በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ በሚል ርዕስ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ በሚል ርዕስ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

             13/9/2017
     ****አዲስ አበባ****

የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሬት በማዕከል እና በክ/ከተማ ደረጃ ለሚገኙ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች  በጊዜ አጠቃቀም ፣ውጤታማ የቡድን የትብብር ችሎታ እና የራስ ተነሳሺነት ወይም እራስን ማስተዳደር በሚሉ ርዕስ ለ3 ቀናት የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው እለት መስጠት ተጀመረ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ስልጠናው ራሳችንን እንድናይ ፣ ስለምንሰራው ስራ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረን ህብረተሰቡን በአውቀት እንድናገለግልና ውጤታማ እንድንሆን የሚያግዝ መሆኑ ገልፀዋል።

የሚሰጠው ስልጠና ባለን አቅም ላይ የበለጠ የሚጨምር ና በቀጣይ ለምንሰራው ስራ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ትኩረት መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።

መረጃው፦ የባለስልጣኑ ከሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments