መንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ ም...

image description
- In code inforcement    0

መንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ ም እና በስነ ምግባር ዙርያ ለሴት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

መንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ ም እና  በስነ ምግባር ዙርያ  ለሴት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

              07/09/2017 ዓ.ም
              ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር  ባለስልጣን  ለባለስልጣኑ የማዕከል ሴት ሰራተኞች "ስነ ምግባር  እና መልካም  አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ " በሚል ርዕስ እና በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ላይ ስልጠና ተሰጠ።

የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰው ኃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሠለሞን ይልማ ሲሆኑ  ስነ_ምግባር ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ አስፈላጊ በመሆኑ እና የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 56/2017ን ማወቅ ሴት ሰራተኞች ለሚገጥማቸው ማንኛውም  የአሰራር   ሰርዓትን በጥሩ ሁኔታ እንዲተገበሩ  ስለሚያደረግ ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ በመግለፅ ስልጠናውን አስጀምረዋል፡፡

"ስነ ምግባር  እና መልካም  አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ  የሰነ_ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ   አማካኝነት ቀርቧል።

በተሰጠው  በስልጠና የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራር ችግር የሚያስከትለው ጉዳት፣ የተቋም ግንባታ ፣ የተጠያቂነት ስርዓት፣ ሴት ሰራተኞች ለተሻለ የመልካም አስተዳደር አገልግሎት በሚሉ የስልጠና ይዘቶች ከባለስልጣኑ ነባራዊ መረጃዎች ጋር  በማጣቀስና ማሳያዎችን  በማቅረብ ተሰጥቷል።

በአዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም ዙርያ የተዘጋጀን የስልጠና የባለስልጣኑ የህግ አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ ኮርሣ  የተሰጠ ሴሆን በስልጠናውም ሰለ መንግስት ሰራተኛ ምንነት፣ ስለ ዲሲፕሊን ቅጣት አወሳሰድ ፣ ሰለ ቅጥር ፣ስለ ጥቅማጥቅም አወሳሰድ ፣ ስለ ቅሬታ ምንነትና አቀራረብ ፣ሰለ መንግስት  ሰራተኛ ግዴታዎች ፣ስለ ዲስፕሊን ቅጣት አይነቶች፣ሰለ ደመወዝ በመሣሠሉት ዙርያ በተበብራራና ግልፅ በሆነ መንገድ  ተሰጥቷል ።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው ከመድረክ ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶባቸው ስልጠናው ተጠናቆል።

ዘገባውን:- የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments