'ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋምና አፈፃጸሙ በ...

image description
- In code inforcement    0

'ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋምና አፈፃጸሙ በማሳደግ ተዓምራዊ ለውጥ በማምጣት ላይ ይገኛል" የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የሰላም፣ የፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ

''ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋምና አፈፃጸሙ በማሳደግ ተዓምራዊ ለውጥ በማምጣት ላይ ይገኛል" የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የሰላም፣ የፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ

              ግንቦት 4/2017
        ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የሰላም የፍትህ መልካም አስተዳደር  ቋሚ ኮሚቴዎች የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የመስክ ምልከታ በማድረግ አፈፃፀሙ ገመገሙ፡፡

በግምገማው  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን በማሳደግ ተምራዊ ለውጥ በማምጣት የከተማ አስተዳደሩን ደንብ ጥሰቶች በመከላከል አዳስ የወጡ ደንቦችን የማስተግበር ትልቅ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀው ይህንንም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ በሎም ማዕከል ላይ በተደረገ የመስክ ምልከታ  እና ሱፐር ቭዥን መመልከታቸውን ተናግረዋል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፉት ዘጠኝ  ወራት ከ3ሺህ በላይ ለሚሆኑ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች  የደመወዝ  ልዮነትና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች መስተካከል መቻሉ ፤ ከድግሪ  በላይ የሆኑ 2000 ምልምል የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አያይዘውም ባለስልጣኑ ለሀገሪቱ ክልል ከተሞች ደንብ የማስከበር ተሞክሮ የመስጠት አስተዎፆ እያደረጉ መሆኑን እና በከተማ አሰተዳደሩ ከሚገኙ አብዛኛው ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ደንብን የማስከበር  ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ  በአቶ ተስፋሁን አሉላ ቀርቧል ።

በሪፖርቱ በርካታ የተቋም  ግንባታ ስራዎች መሰራታቸው  ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስራዎች መሰራታቸውን ፣ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር ሰራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን በሪፖርቱ ቀርቦል፡፡

ከቋሚ ኮሚቴው አባላት  ባለስልጣኑ ከዕለት ወደ እለት እራሱን በማሻሻል አዳዲስ ስራዎችን  በቁርጠኝነት  በመስራት የተለወጠ ደንብ ማሳየት መቻሉን ፣ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየ ያለውን መሻሻል ይበል የሚሰኝ ተግባር መሆኑን በመግለፅ በተለይም  መድረኮች ሲኖሩ ቋሚ ኮሚቴውን በመጋበዝ የሚነሱ ችግሮችን ቀጥታ ቋሚ ኮሚቴው ከሚመለከተው አካል  እንዲወስድ የማድረግ ስራ መሰራቱን የቋሚ ኮሚቴው ተወካዮች ገልፀዋል።

በተጨማሪም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች  ተናበው ሰራዎችን ከሰባዊነት ጋር  በመስራቱ  ለውጦች መመጣታቸውን ጠቁመው በምዘናው አብዛኛው በጥንካሬ አንደሚወሰድ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተቋም ግንባታ እና አዲስ የስገነባውን የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ስቱዲዮ በመጉብኝት ምዘናው ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments