
ባለስልጣኑ ኮሪደር ልማት በመኪና ጉዳት ያደረሰው ሻሞ የመኪና ኪራይ ድርጅት 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
ባለስልጣኑ ኮሪደር ልማት በመኪና ጉዳት ያደረሰው ሻሞ የመኪና ኪራይ ድርጅት 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
03/09/2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ምሽት 2:ዐዐ ሰአት አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ በኮርደር ልማት ላይ ጉዳት በማድረስ የደንብ መተላለፍ የፈፀመ ሻሞ የመኪና ኪራይ ድርጅት 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ።
የደንብ መተላለፉ አዲስ በተስራው በኮርደር ልማት የብስክሌት መንገድ በመኪነና በመሄድ በህዝብ ሀብት ላይ በተሰራው ልማት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ድርጊቱ ከቅጣቱ ባለፈ በህግ ተጠያቂነትንም ስለሚያስከትል አሽከርካሪው ለጊዜው ቢሰወርም በህግ ቁጥጥር ስር ይውል ዘንድ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
በሰዓቱ የተመደቡ ሁለት ኦፊሰሮች በቀጠናው ስራ ላይ ቢኖሩም አፋጣኝ እርምጃ ባለመውሰዳቸው የአንድ ወር ደሞዝ እንዲቀጡ ተደርጓል።
ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments