በባለስልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች...

image description
- In code inforcement    0

በባለስልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምረቃት ማስፈጸሚያ ዕቅድ በተመለከተ ከዩንሸርስቲውና ከባለስልጣኑ ስልጠና አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ

በባለስልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምረቃት ማስፈጸሚያ ዕቅድ በተመለከተ ከዩንሸርስቲውና ከባለስልጣኑ ስልጠና አስተባባሪዎች ጋር  ውይይት ተደረገ

                01/09/2017 ዓ.ም
           ****ይርጋለም/አፖስቶ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በሚሰጠው የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና የምረቃ መርሀግብር በሚመለከት ከባለስልጣኑ እና ከዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመው ንዑስ ኮሚቴ ጋር በማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

የባለስለልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በቅንጅት እየተሰራ ያለው ስራ በስልጠናው ውጤታማነት ላይ ትልቅ አስተዋጾ እያበረከተ እንደሚገኝና በቀጣይም ለሚኖረው የምረቃት መርሀ ግብር ከፍተኛ መነሳሳት ሊፈጥር የሚችል እንደሆነ በመግለጽ ውይይቱን አስጀምረዋል።

የማስፈጸሚያ እቅዱን የባለስልጣኑ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ለንዑስ ኮሚቴው በስልጠና ማጠቃለያ፣ ምዘና፣ መረጃ፣ምደባና ስምሪት ላይ ሰነድ በማቅረብ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም በቀረቡ ሀሳቦች ላይ በኃላፊው ምላሽ በመስጠት እና በዕቅዱ መካተት ባለባቸው ነጥቦች ላይ የጋራ በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል።

ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments