የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከ6ኛ ዙር ዕጩ ፓ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከ6ኛ ዙር ዕጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር በስልጠናው ዙሪያ ውይይት አደረጉ

የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከ6ኛ ዙር ዕጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር በስልጠናው ዙሪያ ውይይት አደረጉ

                    30/08/2017 ዓ.ም
                ****ይርጋለም/አፖስቶ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ እየሰጠ በሚገኘው የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ሂደት ላይ የባለስልጣኑ እና ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመረሮች በተገኙበት ከሰልጣኞች  ጋር ውይይት ተካሄደ። 

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አዲስ ምልምል ሰልጣኙ ስልጠናውን አጠናቆ በቀጣይ ወደ ስራ ሲቀላቀል ለተቋሙ ግንባር ቀደም ሰራተኛ በመሆን ትልቁን አስተዋጾ ያበረክታል ለዚህም ሰልጣኙ በስልጠና ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ስልጠናውን በብቃት ሊያጠናቅቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በስልጠና ወቅት እያለፍን ያለነው ውጣውረድ ለግል ህይወታችንም ሆነ በስራ ላይ ለሚጠብቀን መንገድ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ ቀጣይ የምንወስዳቸው ስልጠናዎችም የበለጠ ብቁ ጠንካራ ሆነን እንድንወጣ ያደርገናል በማለት ሀሳብ ሰጥተዋል።

በተለይ ስልጠናውን እየሰጡ እና እያስተባበሩ ላሉት የባለስልጣኑ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም ከሰልጣኙ ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች በባለስልጣኑ አመራሮች ማብራሪያ በመስጠት ሰልጣኙ ስልጠናውን በተነሳሽነትና በሞራል በመውሰድ የበቃ ኦፊሰር ሆኖ በመውጣት ለተቋሙ ትልቅ ግብአት መሆን እንደሚገባቸው በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል። 

በሳምራዊት ዘሪሁን

ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments