የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አደረገ

የባለስልጣኑ  የስልጠናና ቅድመ መከላከል  ዘርፍ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም  ውይይት አደረገ

                   ሚያዚያ  30/2017 ዓ.ም 
                  ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  የስልጠናና ቅድመ መከላከል  ዘርፍ  የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም እና  የቀሪ ወራት ስራዎች በተመለከተ ከ11 ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና  ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አደረገ።

በውይይቱ  የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በሚያዚያ ወር ድጋፍና ክትትል የታዩ ስራዎች በድክመትና ጥንካሬ  የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር   ወ/ሮ ሠርካለም ጌታሁን ያቀረቡ ሲሆን  በሪፖርቱ  በአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት ውስጥ  የተደረጉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና ስልጠናዎች  ለባለድርሻ አካለት ፣ ለሲቪክ ማህበራት ፣ለበጎ ፈቃደኞች፣ ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ለፖለቲካ አመራሮች እና ለሀይማኖት አባቶች በተለያዮ ርዕሰ ጉዳዮች የተሰጡ ስልጠናዎች ና የግንዛቤ ሰራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

 በተለይ በደንብ ቁጥር 150/2015 ዓ.ም ለማሰፈፀም  ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ.ም እና በወንዞች ዳርቻ ልማት አስመልክቶ በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በመፍጠር የግንዛቤ ስራው ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ እና ውጤቶች መገኘቱ  በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ  በክፍለ ከተማ እና በወረዳ በተደረገ  የክትትልና ድጋፍ ግብር መልስ  ለማሳያነት የሚሆኑ የለሚ ኩራ ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የአዲስ ከተማ እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች  በጥንካሬ እና በክፍተት የነበራቸው ግብረ መልስ  በመድረኩ  ለማቅረብ ተችሎል።

በመጨረሻም በውይይቱ በቀረበው ሪፖርት እና ግብረ መልስ ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የቀጣይ ወራት የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ  ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments