ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ...

image description
- In code inforcement    0

ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ ሰላም የሠፈነባትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ ማድረግ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ ሰላም የሠፈነባትና  የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ ማድረግ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

           ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም 
             ****የአዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2017 ዓ.ም በዘጠኝ ወራት  ውስጥ በቅንጅታዊ ስራዎች የተሰሩ ስራዎችን የገመገመ ሲሆን የከተማውን ሰላም ለማረጋገጥ እና አስተማማኝ ለማድረግ  በትኩረት እየተሰራ ነውም ተብሏል።

በመድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ቅንድታዊ አሰራርን በመዘርጋታችን በከተማው ላይ ሀገራዊና አለማቀፋዊ እንዲሁም ትላልቅ ሀይማኖታዊና ባህላዊ  ሁነቶችን በሰላማዊ መንገድ ማክበር በመቻሉ ሰላም የሠፈነባትና  የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ ማድረግ ተችሏልም ብለዋል ክብርት ኃላፊዋ::

የህዝብ ለህዝብ ትስስርን መፍጠርና ወንጀሎችን ቀድሞ በመከላከል የከተማው  ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ  ከጸጥታው አጋዥ ሀይል ጋር በመቀናጀት ድርሻውን በመወጣቱና ተሳትፎውም እየተሻሻለም መምጣቱን ሀላፊዋ  አንስተዋል ።

ሀላፊዋ አያይዘውም የኑሮ ውድነትን ለመፍጠር አሻጥርን በመዘርጋት ያለ አግባብ ዋጋ በመጨመር የግብይት ስርአቱ በተሳካለት ልክ እንዳይሄድ ያደረጉ ግለሰቦችና የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን፣ የትራንስፖርት ስርዓቱ ምቹ እንዳይሆን ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችም ወደ ስርዓቱ እንዲገቡም የማድረግ ስራ መሰራቱንም አንስተዋል ።

የህዝብ ለህዝብ ውይይቶችን በማጎልበት ዘላቂ ሰላም በከተማው ላይ እንዲሰፍን የሰላም ሰራዊት አደረጃጀቶችን በየግዜው በማጠናከር አካባቢን በንቃት እንዲጠብቁ በማድረግ የጸጥታና የደህንነት ስራ መሰራቱንም  ሀላፊዋ  አንስተው የኮሪደር ልማቱ  መንገድ በብርሃን የተሞላ በማድረግ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏልም ሲሉ ተደምጠዋል ።

አሁን ላይ በከተማው ላይ የህግ የበላይነትና ሰላሟ ለማጽናት በተደረጉ ጥረቶች የመጡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የደንብ ጥሰቶችን መቆጣጠር፣ ወንጀሎችን ማጥፍት ባይቻልም መንስኤዎችን በመለየትና በትብብር በመስራት መቀነስ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል ።

 ሪፖርቱን አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ  ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ም/ኮምሽነር ፍቅሩ አለማየሁ  መጋቢ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሀፊ የቢሮው ም/ሀላፊዎች አማካሪዎች፣የቅንጅታዊ ስራው የተቋማት ሀላፊዎች ተወካዮች ፣የሁሉም ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች እንዲሁም የቢሮው ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments