
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ሂደት ጎበኙ
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ሂደት ጎበኙ
29/08/2017 ዓ.ም
****ይርጋለም/አፖስቶ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ አየተሰጠ የሚገኘው የ6ኛ ዙር የዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአንድ ወር የወታደራዊና የንድፈ ሀሳብ የስልጠና ሂደትን የደረሰበትን ደረጃ የሚመለከት ጉብኝት አደረጉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ለማሀበረሰብ ዘብ የቆመ የደንብ ጥሰትን የሚከላከል የሚቆጣጠር እና ተፈጽሞም ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ የሚወስድ ብቁ የሰው ሀይል መፍጠር የስልጠናው ተቀዳሚ ዓላማ እንደሆነ አንስተው ይህንንም በጉብኝቱ ወቅት መመልከት እንደተቻለ በመጥቀስ ይህ እንዲሆን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በታየው ልክ ወጥ የስልጠና ሂደትን የማስቀጠል ስራው በቅንጅት ሊቀጥል እንደሚገባ አያይዘው ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ኮ/ር ጌቱ ተክለዮሀንስ እንዲሁም የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
አጠቃላይ የአንድ ወር የስልጠና ጊዜ አጭር ሪፖርት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ ኃላፊ ኮ/ር ቦጋለ መሀመድ በወታደራዊ ስልጠና እና የንድፈ ሃሳብ ት/ት አሰጣጥ ዙሪያ እንዲሁም የባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን በስልጠና ወቅት ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ አጭር ሪፖርት በማቅረብ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ላይ የባለስልጠኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በተሰጣቸው ኃላፊነት ሰልጣኙን ለማብቃት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ለሚገኙ የባለስልጣኑ እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና አስተባባሪዎች ምስጋና በማቅረብ በጉብኝቱ የታየው አጠቃላይ የሰልጣኙ አቀባበል እና በቅንጅት የተሰራው ስራ ሊቀጥል እንደሚገባ በማንሳት በቀጣይም ኃላፊነቱን የሚወጣ በስነምግባር የታነጸ ሰልጣኝ ማፍራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ቀጣይ በተጠቀሱት ተግዳሮቶች ላይ በማዕከል እና በዩኒቨርሲቲው መፍትሄ የማስቀመጥ ሂደቱ እንደሚቀጥል በመግለጽ ለምርቃት መርሀ ግብር ከስልጠናው ጎን ለጎን ሊታሰብ እና ስራዎች ሊጀመሩ እንደሚገባ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
በሳምራዊት ዘሪሁን:-
ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments