ባለስልጣኑ ያስገነባውን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ያስገነባውን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮዎች በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ተጎበኘ

ባለስልጣኑ ያስገነባውን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮዎች በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማኔጅመንት  አባላት ተጎበኘ
           
               28/08/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አሰተዳደሩ የሚፈጠሩ የደንብ መተላለፎች ቀድሞ ለመከለከል የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈፀም መመርያዎችን ደንቦችን አዋጆችን ለህብረተሰቡ በሚዲያ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮ  በመገንባት በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን እና በሶሻል ሚዲያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ማዘጋጀት መጀመሩ አስታወቀ።

በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ  ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ያስገነባውን ስቱዲዮ  ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅሙን እያሻሻለ በመምጣቱ በተለይ በከተማችን ላይ  የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም እምርታዊ ውጤቶች ማስመዝገቡ ጠቁመውው ስራዎቹ በህዝብ ግንኙነት ሲደገፉ  የበለጠ እንደሚያጎላው ገልፀዋል።

አክለውም አንድ ተቋም የተሻለ አፈፃፀም የሚኖረው የተቋም ግንባታ ስራ ሲሰራ በመሆኑ ይህንንም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሰው ሀይል፣ በቴክኖሎጂ እና በዘመናዊ የሰራ መገልገያዎች የተደገፉ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑ የስቱዲዮ ግንባታው ስራው አንዱ ማሳያ መሆኑ ተናግረዋል።

በባለስልጣኑ የሚሰሩ ስራዎችን በህዝብ ግንኙነት በማጀብ እና ለማህበሰሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራው አሁን ያለንበት ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ በመግለፅ የሰላምና ፀጥታ ቢሮም እንደተሞክሮ ቀምሮ  ወደ ቢሮው እንደሚወስድ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስገነባውን ዘመናዊ ስቱደዮ በቀጣይ አስፈላጊ ግባቶች በሟሟላት ለማህበረሰቡ በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን እና በሶሻል ሚዲያዎች ሰፊና ተከታታይነት ያላቸው የተደራጀ የግንዛቤ ስራዎች ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮ ስራው ለደገፉና እና ላስተባበሩ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ተልዕኮ በመቀበል ስረውን ለዚህ ያደረሱ ስራተኞችን አመስግነዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments