
ባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ደማቅ የምርቃት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ደማቅ የምርቃት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ውይይት አካሄደ
28/08/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ የሚያሰለጠናቸውን የስድስተኛ ዙር የዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምርቃት ፕሮግራም አስመልክቶ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል ።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ
በኢትዮጽያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በመሰልጠን ላይ የሚገኙ የፖራ ሚሊተሪ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በብቃት አጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡ ያማረና የደመቀ የምርቃት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ከወዲሁ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራት መጀመሩ ጠቅሰው በቀጣይ ቀናቶች ፕሮግራሙ ባማረና በደማቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሰራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።
ባለስልጣኑ ከፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ያሰለጠናቸውን የዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምርቃት ፕሮግራም የተዘጋጀ እቅድ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አቅርበዋል ።
በእቅዱ የስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ሰልጣኞች ስልጠናውን በብቃት አጠናቀው ለስራ ስምሪት ዝግጁ በማድረግ መነቃቃት በመፍጠር እንዲሁም የስራ መመሪያ ለመስጠት ደማቅ የምረቃት ፕሮግራም ለማከናወን የተለያዩ ኮምቴዎች በማዋቀር መታቀዱን ም/ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።
በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በቀረበው እቅድ መሠረት በየዘርፉ የተቋቋሙ ኮሚቴዎችን የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት የምርቃት ፕሮግራሙ ያማረና የደመቀ እንዲሆን የስራ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments