ባለስልጣኑ በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት እቅ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄደ

ባለስልጣኑ በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት  አካሄደ

              25/08/2017 ዓ.ም
               ****አዲስ አበባ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መነሻ በማድረግ በቀሪ  ወራት የሚሰሩ ስራዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከማዕከል አስከ ወረዳ ካሉ አመራሮች ጋር የግምገማዊ ውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በአመራሩ እና ሰራተኛው  ጥረት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በተቋሙ ጥሩ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀው ይህንንም በቀሪ ጊዜያት ያሉንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል አንዳንድ ክፍተቶችን በመሙላት በትጋት በትኩረት ቀንና ሌሊት በመስራት ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ። 

በመድረኩ በቀሪ ወራት በትኩረት መሰራት ያለባቸው ዋና ዋና ተግባራትና መለኪያዎች እቅድ በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል። 

በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ  ስራዎችን ስናከናወን ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠንን ኃለፊነት በመገንዘብ ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ። 

በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ስራዎች በቅንጅት በመሰራታቸው በከተማው የነበሩ የደንብ መተላለፎችንና ህገ ወጥ ተግባራት እንዲቀነስ ማድረግ መቻሉን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ። 

በተጨማሪም በመድረኩ የስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠናና ምርቃት ሂደቱ በተመለከተ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል። 

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments