የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር እጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር እጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በጥብቅ ዲሲፕሊን በእቅዱ መሠረት እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ

የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር እጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በጥብቅ ዲሲፕሊን በእቅዱ መሠረት እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ

                   ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም
                 ****ይርጋለም/አፖስቶ/****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ ሶስተኛ ሳምንት ያስቆጠረው የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ሰልጣኞች የተለያዩ የንድፈ ሀሳብና እና ወታደራዊ ስልጠናዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን በእቅዱ መሠረት እየተሰጠ መሆኑ የስልጠናው አስተባባሪ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ገለፁ።

ሰልጣኞቹ የንድፈ ሀሳብ ስልጠናን ዩኒቨርሲቲው መማሪያ ክፍሎች በጠዋት፣ በከሰዓት እና በማታ ፈረቃ በመከፋፈል እንዲሁም የወታደራዊ ስልጠናን በመስክ በሻለቃ በመለየት በዩኒቨርሲቲው አሰልጣኞች እና በባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪዎች በጋራ የተቀናጀ እና ውጤታማ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ አስረድተዋል ።

በንድፈ ሀሳብ ስልጠና በሶስት ሳምንት ጊዜያት ውስጥ  የህግ ትምህርቶች ፣ የስነ-ምግባርና ሌሎች ተያያዥ ሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ህጎች ላይ መሰረት በማድረግ በቀን ክፍለ ጊዜ እንዲከታተሉ ተደርጓል። 

በስልጠናው በማታ በቀን ክፍለ ጊዜ የጥናት ክፍለ ጊዜ የቡድን ውይይት በማድረግ እርስ በእርስ የመማማር ሂደቱ የማጠናከር ስራ መስራት ተችሏል።

ወታደራዊ ስልጠናው ከመሰረታዊ የወታደራዊ አቋቋም እና ሰላምታ አሰጣጥ ጀምሮ ለመስተካከል እርምጃ ለውጥ፣ ጓድ መሪ ስም ጥራ ፣ ወደ ግራ እና ቀኝ ሰላምታ መስጠት፣ እራስ ቀኝ እራስ ግራ እና  ለመስተካከል ቀኝ ስመር በሚሉ ነጥቦች ላይ ለሰልጣኞች ቅድመ ገለጻ በማድረግ ስልጠና ተሰጥቷል።

የሰልጣኞች በጊቢው ውስጥ የሚኖራቸው ቆይታ ምቹ ለማድረግና ማህበራዊ ግንኙነት ለማጠናከር  የትምህርት፣ የምግብና፣ የሚኒ ሚዲያ፣ የጽዳት፣ የጤና፣ የዲሲፕሊን የስፖርት እና የሴቶች የሰልጣኝ ኮሚቴ በማቋቋም በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል።

በተጨማሪ የሚሠጣቸውን ስልጠና እንዲያጠናቅቁ የሚያስችላቸውን የስነ-ምግባር ት/ት እና ትዕዛዝ አክባሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ወታደራዊ ጨዋነት በተግባር  እንዲተገብሩ በመደረግ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ ባለው ጊዜ ተከታታይ የንድፈ ሃሳብ ትምህርት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ደንቦችና የአፈፃፀም መመሪያዎች እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ደንብና መመሪያ የሚሠጥ ሲሆን በወታደራዊ የመስክ ስልጠና ከሠልፍ በተጨማሪ ለአንድ ወታደር መሠልጠን የሚገባው መሠረታዊ  የአካል ብቃት ስልጠና የሚሠጥ እንደሚሰጥ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ገልፀዋል።

በአጠቃላይ ስልጠናው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚፈለገው እና በሚያስፈልገው ልክ ብቁ የሆነ የሰው ሀይል ለማፍራት  ስልጠናውን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ለማስቀጠል ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ መገለፁ ።

በሳምራዊት ዘሪሁን

መረጃው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments