ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር የ9 ወር...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር የ9 ወር እቅድ አፈፃፀሙ እየገመገ ነው

ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ  ጋር የ9 ወር እቅድ አፈፃፀሙ እየገመገ ነው

                 18/08/2017 ዓ.ም
               ****አዲስ አበባ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ስራዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት በከተማ አስተዳደሩ ባህል አዳራሽ  የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ። 

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በተሰራው ቅንጅታዊ ስራ የወንጀል ምጣኔ እና ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንሱ መደረጉ ገልፀዋል። 

በመርሃ-ግብሩ ላይ  በዘጠኝ ወራት በሁተቱም ተቋማት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገሲሆን በማጠቃለያው ላይ  የቀጣይ ስራዎች የትኩረት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።  

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments